የምድር ሳይሆን የህዝብ ንጉስ 2 ኛ ሳሙኤል 5 ****************************** በዘዳግም መጽሐፍ (17 :15) ውስጥ ንጉሥ እንዴት መሾም እንደሚቻል የሚያሳይ መመሪያ እናያለን ፡፡ ትክክለኛውን እጩ በመምረጥ በአምላክ ላይ ብቻ የሚመረኮዘው ህዝብ ነው ፡፡ ለዚህም ነው ንጉሱ የህዝብ እንጂ የመሬቱ ንጉስ ያልሆነው። በተለይ በአለም ላይ ያሉ ንጉሶችንና አነጋገሳቸውን ስናይ ሁሉም መሬቱን በግላቸው በማዋል ለላው ህብረተሰብ የንጉሶቹ ጭሸኛ እንደሆነ መለስ ቀለስ ብለን የምናነባቸው የታሪክ መጣጥፎች ይነግሩናል።ይህ እንደሚያመለክተው ከዳዊት በላይ ብቸኛው ንጉስ ወይም የግኡዙ ፍጥረት ባለቤት የሆነው ፣ እግዚአብሔር እንደሆነና ዳዊት ግን ህዝቡን የማስተዳደር ውክልና እንዳለው የሚያመለክት ህገ መንግስት ነው፡፡ ይህ ሃሳብ ዛሬ በምናነበው የ II ሳሙኤል ምእራፍ ላይ እናያለን።ጠልቀን ማንበብ ብንችል ከመጀመሪያውም ዳዊትልንገስ ብሎ ሳይሆን ከ ካህኑ ሳሙኤል ምርጫ ጀምሮ ዳዊት ለንጉስነት እንደታጨ እናያለን። በዚህ ምእራፍ ላይም ዳዊት ኬብሮን በነበረበት ሰአት የእስራኤል ነገዶች ወደ ኬብሮን በመምጣት ዳዊት መጥተው ለእርሱ ታማኝ መሆናቸውን ሲያውጁ እናያለን። ይህም የሚያመለክተው የምርጫው ውጤት እንደሚያመለክተው ዳዊት በአብዛኛው ወንበር ማሸነፉን ይገልጽልናል። እነሱ ዳዊት ንጉሥ እንዲሆን የእግዚአብሔርን ፍላጎት ይቀበላሉ ፣ ከዚያ ሽማግሌዎች ቃልኪዳን አድርገው ዳዊትን የእስራኤል ንጉሥ እንዲሆን ቀቡት፡፡ እንግዲህ ይህ የሚያመለክተን ዳዊት ንጉስ ለመሆን በራሱ አላወጀም ግን የህዝቡን ውሳኔ ተቀበለ እንጂ።ለንጽጽር ይሆን ዘንድ ራሳቸውን ንጉስ ለማድረግ በሃብታቸው በጦር ሃይላቸው የሚመኩበአለማችን ያሉ የኖሩ ብዙ ነገስታት አሉ። ይህ ዳዊት የሚያልፈው ሦስ...